The dense forest of Harana, where the black lion is found -->

The dense forest of Harana, where the black lion is found

   የሀረና ጥብቅ ደን The dense forest of Harana, where the black lion is found

 

ኢትዮጵያውያን ለጥቁሮች ነፃነት የከፈሉትን ዋጋ ተከትሎ ጥቁር አንበሶች እየተባሉ ይጠራሉ።

 

ይህ የማንነታችን መገለጫች የሆነው ጥቁር አንበሳ መገኛው ደግሞ ከአዲስ አበባ 570 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በሚገኘው የሀረና ጥብቅ ደን ውስጥ ነው።

 

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ባሌ ዞን ሀረና ቡልቅ ወረዳ የሚገኘው የሀረና ጥብቅ ደን የአከባቢው እስትንፋስ ከመሆን ያለፈ የተፈጥሮ ሚዛን አስጠባቂም ነው ይባልለታል።

 

በዚህ ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ከሚኖሩት የዱር አራዊት ውስጥ መጠርያችን እና መሞጋገሺያ ስማችን የሆነው ጥቁር አንበሳ ተጠቃሽ ነው።

 

የአከባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ይህንን ጥቁር አንበሳ ጠዋት እና ማምሻውን ከጎሬው ወጥቶ ተፈጥሮ በሰጠችው ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ሲገማሸር መመልከት ይቻላል።

 

The dense forest of Harana, where the black lion is found


የሀረና ጥቅጥቅ ደን የአከባቢ ስነ-ምህዳርን በመጠበቁ በካርቦን ሽያጭ ውስጥ ተካቶም ይገኛል።

 

አርሶአደር ከድር ጅብሪል የአከባቢው ነዋሪ ሲሆኑ አባቶቻችን ከደኑ እንጨት አይደለም ሀረግ አይቆርጡም ነበረ እኛም ያንን በማስቀጠል ደኑን እየጠበቅነው እንገኛለን ብለዋል።

 

ደኑ ለኛ ልባችን ነው የሚሉት አርሶአደር ከድር፤ በሀረና ወረዳ ውስጥ 16 ቀበሌዎች አሉ እያንዳንዱ ቀበሌ ካርታ አለው እስከ 10 ሄክታር የሚሸፍኑ ቀበሌዎች አሉ በነሱ ውስጥም 7 ሰዎች ተመርጠው ደኑን ይጠብቃሉ ያስተባብራሉ ስለደኑ ያስተምሩናል ሲሉ ነው የገለፁት።

 

በካርቦን ንግድ ክፍያ ስርዓት ውስጥ 2014 . የገባው የሀረና ደን በዛው ዓመት ብቻ 1.5 ሚሊየን ብር፤ 2015 . ደግሞ 7 ሚሊየን ብር አስገኝቷል።

 

አርሶአደር ከድር እንደሚሉት በካርቦን ክፍያው በአከባቢው ወፍጮ ተተክሏል ቡና ወደ መካከለኛ ገበያ ለማቅረብ ተችሏል።

 

የሀረና ጥቅጥቅ ደን በተፈጥሮ ሀረግ ጥልፍ የተሸመነ የሚያስደምም መልክአ ምድር የተላበሰ ቦታ ሲሆን፤ በውስጡ አፈሩን ይዘው የማይሄዱ ኩልል ያሉ ብዙ ወራጅ ወንዞች ይገኙበታል።

 

የሀረና ጥብቅ ደን ወደ ካርቦን ሽያጭ ስርዓት የገባው ጥበቃው የተስተካከለ እና ሰፊ መሬት በመያዝ ለአካባቢ አየር ጥበቃ የሚያደርገው አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ ነው ብለዋል የሀረና ቡልቅ ወረዳ አከባቢ ጥበቃ /ቤት ኃላፊ መሀመድ ከድር።

 

ለአርሶአደሮቹ ክፍያው ደርሶ ለልማት እንዲውል የሚያደርግ ማህበር ተቋቁሞ በስራ ላይ እንደሚገኝ የገለፁት ኃላፊው፤ ገንዘቡም ደኑን ለመጠበቅ ለአከባቢው ልማትና ለችግኝ ጣቢያ ይውላል ሲሉ ጠቁመዋል።

 

የሀረና ጥቅጥቅ ደን የምድር ሳንባ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም።

 

ያደጉ ሀገራት ከተለያዩ ፋብሪካዎቻቸው በሚያወጡት በካይ ጋዝ አለም የአየር ንብረቷ ሲጎዳ በቀጥታ የገፈቱ ቀማሽ የሚሆኑት ደግሞ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ናቸው።

 

አሁን ላይ ከሞላ ጎደል በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት የተፈጥሮን ሚዛን ጠባቂ ለሆኑ ጥቅጥቅ ደኖች የካርቦን ክፍያ ስርዓት ተዘርግቶ ይገኛል።

 

አሁንም ግን ምድርን በሚዛን እያሻገሩ የሚገኙት እንደሀረና ያሉ ጥቅጥቅ ደኖች ናቸውና ነገ የተሻለ የአየር ንብረት እንዲኖር ምርታማነትን ለመጨመር አካባቢን ለመጠበቅ ችግኞችን መትከል አግባብ ነው።

 

ምንጭ:-ኢቲቪ

 

buttons=(Accept !) days=(20)

Our website uses cookies to enhance your experience. Learn More
Accept !
To Top