ጨበራ ጩርጩራን በጨረፍታ/ At a glance Chebera-Churchura National Park -->

ጨበራ ጩርጩራን በጨረፍታ/ At a glance Chebera-Churchura National Park

 

👉የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በኮንታና በዳውሮ ዞኖች መካከል ይገኛል

 

👉ብሔራዊ ፓርኩ 1997 . በኮንታና በዳውሮ ህዝቦችና አስተዳደር አካላት ጥያቄና ተሳትፎ መሰረት ነው በብሄራዊ ፓርክ ደረጃ የተቋቋመው


https://www.tripsethiopia.com/at-glance-chebera-churchura-national

 

👉ፓርኩ የሚያካልለው የቆዳ ስፋት 1410 ካሬ ኪሎ ሜትር ስኩዌር ሲሆን በመካከለኛው ኦሞ ሸለቆ ውስጥም ይገኛል

 

👉ብሔራዊ ፓርኩ ከመዲናችን አዲስ አበባ 475 / ርቀት ላይ ይገኛል

 

👉ፓርኩ የግዙፉ የአፍሪካ ዝሆን መኖሪያም ሲሆን በውስጡ 800 በላይ የሚሆኑ ዝሆኖችና 5,000 በላይ ጎሾች የሚገኙበት መሆኑ ፓርኩን ልዩ ያደርገዋል

 

👉40 ትላልቅና መካከለኛ አጥቢ እንዲሁም 18 ትናንሽ አጥቢ የዱር እንስሳት ዝሪያዎች ይገኛሉ

 

👉በጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ እንደ አጥቢዎቹ ሁሉ የበርካታ አዕዋፋት ዝርያዎች መኖሪያ ነው

 

👉እስካሁን በተጠናው ውስን ጥናት ብቻ 137 የአእዋፍ ዝርያዎች ተለይተዋል፤ከእነዚህም ውስጥ 6 በሀገራችን በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ናቸው

 

👉106 እንጨታማ የእጽዋት ዝሪያዎች የሚገኝበት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ስድስቱ የእጽዋት ዝርያዎች በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ናቸው፤በተጨማሪም በውስጡ ከሚገኙ የዱር ዕፅዋት ዝሪያዎች መካከል ዝንጅብል፣ቡና፣ኮረሪማ፣ እንሰት፣እጣንና የጌሾ ዝርያዎች ዋና ዋናዎቹ ናቸው ፡፡

 

👉በፓርኩ ውስጥ ብቻ 6 ሀይቆች የሚገኙ ሲሆን ባሄ፣ ቡሎ፣ሺታ፣ ቆቃ፣ከሪቤላና ጮፎሬ እጅግ አስደናቂና ሊጎበኙ የሚገቡ በብሔራዊ ፓርክ ውስጥ የሚገኙ ሐይቆች ናቸው

 

👉በብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ከሚገኙ ሐይቆች በአንዱ ብርቅዬ ወርቃማ የዓሳ ዝርያ የተገኘ ሲሆን በዓለም ሊቃውንት እውቅና አግኝቶ በሳይንሳዊ ስሙ ጋራ ጨበራ በመባልም ይጠራል

 

👉ከብሔራዊ ፓርኩ ገፀበረከቶች መካከል ለአብነት ፏፏቴዎች፣ፍልውሃዎችና የማዕድን ውሃዎች የሚጠቀሱ ናቸው

 

👉ብሔራዊ ፓርኩ በአሁኑ ሰዓት በገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት እየለማ የሚገኝ ሲሆን ቱሪስቶች ብዙም ሳይጉላሉና ሳይለፉ በቀላሉ ጎብኝተው እንዲመለሱ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠሩም ባለፈ ፓርኩን በተገቢው ሁኔታ ለማስተዳደርና የዱር እንስሳትን በቅርበት ለመከታተልና ለመጠበቅ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል

 

ምንጭ ፦የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ




buttons=(Accept !) days=(20)

Our website uses cookies to enhance your experience. Learn More
Accept !
To Top